አገልግሎቶች

የስታርትአፕ ድጋፍ

ነጻ የገንዘብ ድጋፍ፣ የብድር ዋስትናና በአነስተኛ ምጣኔ የሚቀርብ የብድር ሥርዓት ማዘጋጀት፤ የንግድ ስራ ስትራቴጂ እና የገበያ ትስስር መፍጠር፡ የገበያ ጥናትና ምክር፤ ከአዳዲስ ካፒታል /መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ጋር ማዛመድ፤ የማስተዋወቅ፣ አብረው እንዲሰሩ፤ የገበያ አማራጭ እንዲፈጠርላቸው ማድረግ፣የስታርታፕ ከባቢያዊ ሥርዓት ገንቢዎችንና ኢንቨስተሮችን ጠንካራ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሥርዓት በመገንባት ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ የስልጠና፤ ማማከርና ቴክኒክ ድጋፍ መስጠት የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማካሄድ ፡፡ የስታርታፕና የኢኖቬቲቭ የንግድ ድርጅቶች መለያን ለማግኘት የሚያስችለ ማመልከቻዎችን ይቀበላል፤  የቀረቡ ማመልከቻዎችን ይመረምራል፣ በዚህም መሠረት መለያዎችን ይፈቅዳል፡፡

የፕሮቶታይፕ ደረጃ ደጋፍ

አገልግሎትና ምርት መሆን የሚችሉ ቴክሎጂዎች ከሃሳብ ጀምሮ እንዲደገፉና እንዲለሙ ማድረግ፡፡ የፈጠራ ሀሳብ ያላችው ባለሙያዎችን  በኢንኩቤሽን ማእከላትን የሃርድዌር እና ሶፍትዌር ዲዛይን፤ የምርትና አገልግሎት ፕሮቶታይፖች እንዲወጡ ማድረግ፤ ጥራት ያላቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ ለፕሮቶታይፕ ስራዎች የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፤ መሰረተ-ልማት (የስራ ቦታ፤ ኮምፒውተሮች፤ ኢንተርኔት፤ ላቦራቶሪዎች ወዘተ)፤ በማቅረብና አመራር በመስጠት ማገዝ፣ የስልጠና፤ ማማከርና ቴክኒክ ድጋፍ መስጠት የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማካሄድ 

ተቋማትን ማጠናከር

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ተቋማትና ባለሙያዎች አቅም ግንባታን ይደግፋል፤ የሙያ ማኀበራትንና አካዳሚዎችን ይደግፋል፣ ያበረታታል፤

ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻል፣ ለማሳደግና ለገበያ ለማቅረብ የሚደረጉ ጥናቶችን፣ የምርምርና ስርጸት ሥራዎችን ያበረታታል፣ ወደተግባር እንዲሸጋገሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መዳበር የበለጠ አስተዋጽዖ ሊያደርጉ  የሚችሉ ግለሰቦችን፣ የሙያ ማኀበራትንና አካዳሚዎችን ያበረታታል፣ ይደግፋል፤

ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማትና ለፈጠራ ሥራዎች ዕድገት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማትና ማበረታቻ የሚሰጥበትን ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፤

የስታርት አፕ ምዝገባ ሂደት

 የስታርታፕ የንግድ ድርጅት መለያ ምልክት ለማግኘት የሚከተለት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፣ 

(ሀ) ድርጅቱ ወደ ገበያ ይዞ ሊገባ የሚፈልገው ምርት፣ ምርት የማምረት ሂደት፣ ወይም አገልግሎት ኢኖቬቲቭ መሆን ወይም በወቅቱ ያለውን የምርት፣ የአገልግሎት ወይም የገበያ መዋቅር የሚለውጥ፤

 (ለ) ድርጅቱ ተጨማሪ ካፒታል ሲያገኝ ሊያድግ የሚችለ፣ እንዲሁም ተጨማሪ ድርጅት ማቋቋም ሳያስፈልገው የምርቱንና የአገሌግልቱን አቅራቦት ማስፋት የሚችለ፤

 (ሐ) ቢያንስ የድርጅቱ 51% ካፒታል የኢንተርፕሬነሩ የግል ድርሻ፣ 

(መ) የንግድ ድርጅቱ ጥቃቅን፣ አነስተኛ፣ ወይም መካከለኛ ኢንተርፕራይስ፤ እና

 (ሠ) የንግድ ድርጅቱ ከተቋቋመ አምስት ዓመት ያልሞላው፤ መሆን ይገባዋሌ።

የስታርታፕ የንግድ ድርጅት ቅድመ ምዝገባ 

(1) የስታርታፕ የንግድ ድርጅት ለመመሥረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው፣ በዚህ አዋጅ የተደነገጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያሟላ የስታርታፕ የንግድ ድርጅት መለያ ምልክት ለማግኘት ሚኒስቴሩ ጋር ቀርቦ ማመልከቻውን ማቅረብ ይችላል። 

(2) ቅድመ ምዝገባ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 13 እና 14 የተደነገጉትን የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባና የንግድ ምዝገባ ለመፈጸም አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው።

 (3) የቅድመ ምዝገባ ማመልከቻና አባሪ ሰነዶች መቅረብ ያለባቸው በዲጂታል መንገድ ነው፤

 (4) በዚህ አንቀጽ ውስጥ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ሚኒስቴሩ የቅድመ ምዝገባ ምስክር ወረቀት መስጠት አለበት። (5) በዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች መሠረት የሚካሄድ የምዝገባ ሂደት በአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ አለበት። 

(6) ቅድመ ምዝገባ የሚያገለግለው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው።

የስታርታፕ የንግድ ድርጅት የንግድ ሥራ ምዝገባ

 (1) የስታርታፕ የንግድ ድርጅቶች የቅድመ ምዝገባ ዘመናቸው እንደተጠናቀቀ የንግድ ምዝገባ ማከናወን አለባቸው።

 (2) የምዝገባ ማመልከቻና ለማመልከቻው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች የሚቀርቡት በዲጂታል መንገድ ነው።

 (3) የስታርታፕ የንግድ ድርጅቶች ምዝገባ በንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ይከናወናሌ። 

(4) ምዝገባን በተመለከተ የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ተገቢ የሆነ ቅድመ ሁኔታዎችን ይስተናገዳሉ። 

(5) በዚህ አንቀጽ ዴንጋጌዎች መሠረት የሚካሄድ የምዝገባ ሂደት በአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ አለበት።

የስታርታፕና የኢኖቬቲቭ የንግድ ድርጅቶች ግዴታዎች

  1. የስታርታፕና የኢኖቬቲቭ ድርጅቶች 

(ሀ) ሊያሳካ ያቅደውን የዕድገትና የሥራ ዕድል ብዛት የማሳካት፣

 (ለ) የሒሳብ አያያዛቸውን ሕጋዊ አሠራርን የተከተለ መሆኑን የማረጋገጥ፣ እና 

(ሐ) የንግድ ድርጅቱ የሕግ ቅርጽ ሲቀይር ይህንኑ የማሳወቅ ግዳታ አለበት።

 (2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተዘረዘሩ ግዴታዎች ሲጣሱ እንዳግባብነቱ የስታርታፕ የንግድ ድርጅትና የኢኖቬቲቭ የንግድ ድርጅት መለያ ሠርተፊኬት ይሰረዛል። 

(3) በዚህ አዋጅ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች በቀጣይነት ያልተሟላ ከሆነ፣ የስታርታፕ የንግድ ድርጅት መለያ ወይም የኢኖቬቲቭ የንግድ ድርጅት መለያ ምልክትን ለመሰረዝ በቂ ምክንያት ተደርገው ይወሰዳሉ።

 (4) በዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች መሠረት ውሳኔ የሚሰጠው ውሳኔው የሚያርፍበት ድርጅት የተጣለበትን ግዴታዎች ያልተገበረበትን ምክንያት በተመለከተ መልስ እንዲሰጥ ዕድል ይሰጠዋል፡፡ ከተሰጠው በኃሊ ነው።

 (5) የስታርታፕ የንግድ ድርጅት መለያና የኢኖቬቲቭ የንግድ ድርጅት መለያ የሚሰረዙበት አግባብ ዝርዝር በሚኒስቴሩ  መመሪያ ተካተዋል።

Contact address for start up

Name: negede yisihaq

Phone: 0911661675

Email : nyisihaq@yahoo.com

Name: alazar sisay

Phone: 0911486424

Email: alazar.sisay1@gmail.com